እ.ኤ.አ በ 2018 በግምት 570 000 የሚሆኑ ሴቶች በዓለም ዙሪያ በማህፀን በር ካንሰር የተያዙ ሲሆን ወደ 311 000 የሚሆኑ ሴቶች በበሽታው ሞተዋል ፡፡ የማያቋርጥ ኢንፌክሽን ያለው ከፍተኛ ጎጂ የሆነ የሂውማን ፓፒሎማቫይረስ (HPV) የማኅፀን በር ካንሰር ዋና መንስኤ ነው ፡፡
የኤችፒ..ቪ ቫይረስ ዓይነቶች 16 እና 18(HPV strains 16 and 18) ብቻ 70% ለሚሆኑት የማህፀን በር ካንሰር በሽታዎች አምጪ ናቸው ፡፡ አብዛኛው የኤችፒ..ቪ ኢንፌክሽን በግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፉ ናቸው ፡፡
በተጨማሪም በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ምንም አይነት ምልክቶች የላቸውም ፣ ይህም ሳያውቁት ቫይረሱን እንዲያሰራጩ መንስኤ ይሆናል ፡፡ ዕድሜያቸው ከ 30ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ ሴቶች የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ በኮቴስቲግ(co-testing) ማድረግ አለባቸው ፡፡
የኮቴስቲግ ምርመራው የኤች.ፒ.ቪ ዲ ኤን ኤ ምርመራ እና የፓፕ ስሚር (ሳይቶሎጂ) ጥምረት ነው። ምርመራዎቹ ቫይረሱን ለይቶ ለማወቅ ይረዳሉ እንዲሁም ለወደፊት ካንሰር ሊሆኑ የሚችሉ ያልተለመዱ ህዋሳትን በተመሳሳይ ጊዜ ይመለከታል ፡፡ ስለሆነም ይህ ዘዴ ሐኪሙ የማኅጸን ጫፍ ካንሰርን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ በፓፕ ብቻ ከመርመር የበለጠ ለይቶ ለማወቅ ይረዳዋል ፡፡
የኮቴስቲግ ምርመራ በየ3-5 ዓመታት ቢያገኙ ይመከራል ፡፡ ግን ውጤቱ ጤናማ ካልሆነ እንደ ዶክተር ምክር ክትትል መደረግ አለበት ፡፡
For more information please contact:
Last modify: ኖቬምበር 13, 2024