ታካሚዎች በማንኛውም ጊዜ በተለይ የካንሰር ህክምና የሚከታተሉ ታካሚዎች የስነልቦና ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡ የካንሰር በሽታ ታካሚዎች በአካልም ሆነ በስነ-ልቦና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማግኘት ያስፈለጋቸዋል፡፡ እነዚህ ታካሚዎች በቡምሩን ግሬድ ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኙ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ የሆስፒታሉ ፋርማሲስቶች ወይም የመድሃኒት ቀማሚ ባለሙያዎች በተቻለ መጠን አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የታካሚውን ፍላጎት ለማሟላት ይሰራሉ፡፡ በማንኛውም መንገድ ታካሚዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታላችን ሲመጡ ተገቢ ህክምና እና ፈገግታ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ ማበረታቻዎች በመስጠት የህክምና አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ምክንያቱም በሆስፒታላችን ጥሩ ስነልቦና ህክምና ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው በመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም የዚህ አይነት የህክምና አገልግሎት ሆስፒታላችን የተመሰገነ ሆስፒታል ነው፡፡ ኒራቾርን ኩቾንተራ በገለፀችው መሰረት በሆስፒታሉ የመድሃኒት ቀማሚዎች ወይም የመድሃኒት ማምረቻ ባለሙያዎች ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ የነበራቸውን አመለካከት እና ሲያደርጉ የነበረውን ጥንቃቄ እና ሲሰጡ የነበረውን እንክብካቤ በሆሪዞን ክልል የካንሰር ማእከል ውስጥ ከፍተኛ እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ሲሰጡ እንደነበሩ አብራርተዋል፡፡
ከመድሃኒት ቅመማ አገልግሎት በላይ
በሆሪዞን የካንሰር ህክምና ማእከል የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት በተለይ ዋናው እና አብይ ህክምና ስራዎች በመድሃኒት ቀማሚዎች ጫንቃ ላይ ሲሆን እነዚህም ተገቢ የህክምና አገልግሎት እና አስፈላጊ መድሃኒት በእያንዳንዱ የካንሰር ታማሚ የህመም ደረጃ እና መጠን መሰረት አዘጋጅቶ ማቅረብ ነው፡፡
የህክምና አገልግሎት አሰጣጡን አንዳንድ ጊዜ ከባድ መድሃኒቶች መስጠትን ጨምሮ የሚከናወን በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ ታካሚው ሆነ የህክምና አገልግሎት ሰጪው በተገቢው ሁኔታ ተዘጋጅተው የተፈለገውን አገልግሎት ለማግኘት እና ለመስጠት ዝግጁ በመሆን የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር አስፈላጊ ጥረት ማድረግ የሚገባቸው በመሆኑ ከፍተኛ ክህሎት ያላቸው እና በዘርፉ የተካኑ ልዩ ባለሙያዎች በተለይ የመድሃኒት ቅመማ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ልዩ ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋሉ፡፡ በሆስፒታላችን የኬሚካል ህክምና ብቻ በመስጠት ላይ የተሰማራ ሳይሆን እንዲሁም የበሽታ መቋቋም አቅም የማዳበር ስራ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሳይሆን ከዚህ በተጨማሪም እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ የታዘዙ የሕክምና እና የመርፌ አገልግሎትም መስጠትም የሚጨመር መሆኑን፤ ንራኮን አብራርተዋል፡፡
‹‹በአጠቃላይ በመጀመሪያ ደረጃ ታካሚው ተመርምሮ የምርመራ ውጤቱ ከተረጋገጠ በኋላ ታካሚውን ተቀብለን አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠጥ ከሁለት ሳምንት በላይ አይፈጅብንም፡፡ አብዛኛው ጊዜ ህክምናው በአንዳንድ የሰውነታችን የስሜት ህዋሳት ህክምና ላይ የተመሰረቱ ቢሆንም በጥንቃቄ በዘርፉ በሰለጠነ ባለሙያ እና ልዩ ስልጠና በተሰጠው አካል በተለይ በሰውነታችን ህዋሳት ህክምና አገልግሎት እና ሌሎች ኤፓታሎጂስት፣ የጋስትሪት ህክምና ወይም ተያያዥ ህክምና አገልግሎት በጥንቃቄ በዘርፉ በሰልጠኑ ባለሙያዎች የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡ በምርመራው ሂደት ታካሚው የካንሰር ተጠቂ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ለከፍተኛ እና ለተሻለ ምርመራ ወደ ሌላ ቀጣይ የምርመራ አገልግሎት ተልኮ ለመጨረሻ ጊዜ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ከዚያም በኋላ በሽታው የሚገንበት ደረጃ በምርመራ ከተለየ በኋላ የተለያዩ መሰጠት የሚገባቸው ህክምና አገልግሎት እንደበሽታው ደረጃ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ህክምናው መሰጠት ከመጀመሩ በፊት በቅድሚያ ታካሚው እና ሀኪሙ ስለሚሰጠው የህክምና አገልግሎት እና አመቺ የህክምና አሰጣጥ ሁኔታ ላይ ተገናኝተው እና ተቀራርበው የሚወያዩበት ይሆናል››፡፡
በመቀጠልም ስለ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሀኪም እና በታካሚው ወይም በታካሚው ቤተሰቦች መካከል ስለ የህክምናው አሰጣጥ ውሳኔ ላይ የጋራ ስምምነት ላይ የሚደረስ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም በመካከላችን የተለያዩ የካንሰር ህክምና አሰጣጥ አገልግሎቶች ስላሉ እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪ እና የህክምና አሰጣጥ ሁኔታ ስለሚከተሉ የራሳቸው የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ስላላቸው በተለይ በህምመሙ ወይም የካንሰር አይነት እና ባህሪ ላይ የተወሰነ የህክምና አይነቶች የራሳቸው አሉታዊ ተፅዕኖ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህ ወቅትም ታካሚው ሙሉ በሙሉ ስለህክምናው አገልግሎት አሰጣጥ ጥቅም እና ጉዳት መረዳቱን ሀኪሙ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ በህክምና ወቅትም ታካሚው ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ጋር መላመድ እና ቢያንስ ከጉዳቱ ይልቅ የህክምናው ጥቅም በታካሚው ላይ ያመዘነ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ጊዜም ውሳኔው በታካሚው ከተወሰነ በኋላ ሃኪሙ፣ የመድሃኒት ቀማሚ ባለሙያ በጋራ በመሆን ስለሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ላይ ተገቢ ማብራሪያ ማዘጋጀት እና መስጠጥ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰጡ መድሃኒቶች እና የህክምና አገልግሎቶችን ትክክለኛ መጠን፣ የመድሃኒቱ ሁኔታ የሚሰጥበት ጊዜ፣ የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅእኖ እና የሚሰጠው ጥቅም በአግባቡና በተገቢው ሁኔታ በዝርዝር ተዘጋጅቶ በመረጃ ቋት ተመዝግቦ መቀመጥ ያስፈልጋል፡፡፡ ይህ አሰራርም ሌላ ስለ ህክምናው አገልግሎት መረጃ ማወቅ ለሚፈልገው በማንኛውም ጊዜ ግልፅ መረጃ መስጠት እንዲቻል ለማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታካሚው የአመጋገብ ሁኔታ እና የምግብ አወሳሰዱ ሁኔታ ከህክምና አሰጣጡ ጋር ተዳምሮ በታካሚው ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖ ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው፡፡
ውሳኔ ላይ ከተደረሰ በኋላ እና ህክምና እና መድሃኒት ታዞ ወደ ህክምና አገልግሎት መስጠት ከተገባ በኋላ የመድሃኒት ቀማሚው ስራ በተገቢው ሁኔታ የሚሰጠውን የመድሃኒት መጠን በአግባቡ መወሰዱን በየጊዜው ማረጋገጥ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑትን የህክምና አገልግሎቶች ተያይዘው የሚሰጡ መሆናቸውን ከሰውነት የሚወጡ ፈሳሾች በታዘዘው መድሃኒት መሰረት በአግባቡ መሆናቸውን ማጣራት ይኖርበታል፡፡ ምናልባት አልፎ አልፎ የሚወሰድ ከሆነ ወይም ያለው ሁኔታ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ ተገቢ መድሃኒት እና የህክምና አገልግሎት የሚገኝበት ሁኔታ የመድሃኒት ባለሙያው በማፈላለግ መኖሩን አረጋግጠው ታካሚው ህክምናው እንዲጀምር የማድረግ ሃላፊነት አለበት፡፡ በእርግጥ የታዘዘውን መድሃኒት እንደገና አናጣራም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የመድሃኒቱ አሰጣጥ ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የማድረግ ሃላፊነት ያለብን ሲሆን የእያንዳንዱ የታካሚ የወቅቱ የጤና ሁኔታ በተለይ በነጭ እና ቀይ የደም ሴሎቻቸው ጋር የተያያዙ የጤና ሁኔታዎች ከኩላሊታቸው እና ከጉበታቸው የጤና ሁኔታ እና አገልግሎታቸው ጋር ተያይዞ ማጣራት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የህክምና እና የሚሰጠው መድሃኒት ማስተካከል አስፈላጊ መስሎ ከታየ የካንሰር ህክምና ባለሙያ ወዲያው ስለጉዳዩ አውቆ አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይገባል፡፡ ከዚህ በኋላ አስፈላጊውን እርምጃ ከወሰደ በኋላ የህክምና አገልግሎቱ መሰጠት እንደሚጀምር ንራኮርን በሰጡት ማብራሪያ የዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት ያለው የመድሃኒት አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
መድሃኒት ከመስጠት በላይ
ለካንሰር ህክምና አገልግሎት መድሃኒት በሚሰጥበት ጊዜ ከምንም በላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው መድሃኒቱ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተፅእኖ እና የጎንዮሽ ጉዳት መሆኑን እና ይህ ደግሞ ከመድሃኒት መድሃኒት እንደሚለያይ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ታካሚው አዲስ የህክምና አገልግሎት በሚጀምርበት ጊዜ ወይም ሌላ ዙር ህክምና በሚጀምርበት ጊዜ ወይም ህክምና መሰጠት በሚጀምርበት ጊዜ የመድሃኒት ባለሙያዎች ታካሚውን በዚሁ አንፃር ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡ በእኛ መካከል በዚህ ሙያ የተካኑ የመድሃኒት ባለሙያዎች ያሉ ሲሆን እነሱም ተገቢ የህክምና አሰጣጥ እና ዝርዝር መድሃኒቶችን ለታካሚዎች ያብራራሉ፡፡ ከአለም አቀፍ የሚመጡ ታካሚዎች ታይን የማይረዱ ከሆነ በፈለጉት የህክምና ዙሪያ አስፈላጊውን እና የተቀናጀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ አስተርጓሚ በመጠቀም የፈለጉትን የህክምና አገልግሎቶች ያማስገንዘብ ስራ እንሰራለን፡፡ ለአንዳንድ ታካሚዎች የአመጋገባቸው ስርአት እና ግብአቶች የታካሚውን ጥንካሬ ለመገንባት አስፈላጊ መሆናቸውን ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የረጅም ጊዜ ህክምና በሚያስፈልግበት ጊዜ መቋቋም እንዲችሉ ተገቢ የአመጋገብ ስርአት እንዲከተሉ ይደረጋል፡፡ የታካሚው አካል ለህክምና አገልግሎት መስጠት ዝግጁ ሆኖ ካልተገኘ፣ ህክምናው ከሚሰጠው ጥቅም ልክ ለጉዳት የበለጠ የሚያጋልጥ ሆኖ ከተገኘ አስፈላጊው የህክምና አገልግሎት እርምጃ ይወሰዳል፡፡
አንዳንድ ታካሚዎች በሚታዘዝላቸው መድሃኒት ምክንያት የእንቅልፍ ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ ወይም በጣም በከፍተኛ እንቅልፍ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ላካንሰር ታካሚ ደግሞ በቂ እንቅልፍ አስፈላጊ እና ወሳኝ በመሆኑ ምክንያት የደም ህዋሳት በተለይ ከእኩለ ለሊት እስከ 10 ሰዓት ድረስ እንዲመረት ይደረጋል፡፡ በዚህ ሰዓታት ውስጥ ታካሚው መተኛት ካልቻለ መድሃኒታቸውን መውሰድ አይችሉም፡፡ ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ በለሊት ታካሚው በቂ እንቅልፍ የሚተኛ መሆኑን እና ያለመሆኑን በቅድሚያ ጠይቀን እናጣራለን፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የእንቅልፍ መድሃኒት እንዲወሰድ ይደረጋል፡፡ ጉዳዩ በጣም ስለሚመለከተን ለእያንዳንዷ ሂደት ከፍተኛ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ ኒራኮርን በዚህ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ስራ ሂደት የ15 ዓመት የስራ ልምድ ያላት ሲሆን በህክምና ማእከላችን የበርካታ ስራ ባልደረቦችን ታማኝነት ያተረፈች እና ስለህክምና አሰጣጧ ጋር ተያይዞ በርካታ ታካሚዎች አገልግሎቷን ይወዱላታል፡፡ የምትሰጠው የአስተዳደር አገልግሎት ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎንም የመድሃኒት ቅመማ ስራ አገልግሎት በጣምራ የምትሰራ ሲሆን በሆሪዞን የካንሰር ህክምና ማእከል ከፍተኛ እና ሰፊ አገልግሎት ከልባቸው በትክክል ከሚሰጡ የማእከሉ የስራ ባልደረቦች መካከል አንጋፋዋ እና ግንባር ቀደም በመሆኗ ብዙ ጊዜ የካንሰር ታካሚዎች ጤና ከምንም በላይ ተሽሎ ይወጣሉ፡፡ ብዙ ጊዜ በዘላቂነት የስራ ባልደረቦቿ የምታስተምረው የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሲሆን በዘርፉም በቂ ሙያ እና ክህሎት እንዲያዳብሩ ወይም ለማዳበር ጥረት እንዲያደርጉ ትመክራቸዋለች፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የስራ ባልደረቦቿ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ ምክር ትሰጣቸዋለች፡፡ እንዲሁም የስራ ባልደረቦቿ ከምንግዜውም በላይ በስራቸው ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆኑ እና ከተለመደው ጊዜ በላይ የመስራት ባህሪ እንዲያዳብሩ ትመክራቸዋለች፡፡ ኒራኮርን እያንዳንዱ ሰራተኛ ምንግዜም ለምን እንደሚሰሩ ማወቅ እንዳለባቸው ወይም ማስታወስ እንዳለባቸው ትመክራቸዋለች፡፡ ‹‹ሁላችንም በቡድን ሆነን ስንሰራ ታካሚዎች በጣም ውስን እድል ያላቸው መሆኑን ተገንዝበን ሁልጊዜም ከካንሰር በሽታ ጋር እየታገሉ እና በበሽታው እየተሰቃዩ የሚኖሩ መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ እዚህ የሆንበት ምክንያት ታካሚዎቻችንን በጥንቃቄ ለመርዳት መሆናችንን አውቀን ከዚህ በላይ ከፍተኛ ርቀት በመጓጓዝ ለስራችን ትኩረት መስጠት ይገባናል፡፡ ምንግዜም የታካሚዎቻችን ጤና ተሽሎ ለማግኘት መስራት አለብን፡፡ ስለሆነም ከህመማቸው ድነው በመልካም ኑሩ እንዲኖሩ መስራት ይኖርብናል›› ብላለች፡
For more information please contact: