bih.button.backtotop.text

አዳዲስ የጡት ካንሰር ሕክምናዎች በሆራይዘን ብቅ ብለዋል

“ከዓለም ቀዳሚ ካንሰር ባለሙያዎች የተገኘ የምስራች ዜና ለጡት ካንሰር ህመምተኞች አዲስ ተስፋን ይሰጣል፡፡”

The U.S. Food and Drug Administration (FDA) የቆየና የተሰራጨ የጡት ካንሰር ላለባቸው ታካሚዎች alpelisib የተባለውን መድሀኒት  fulvestrant ከተባለው መድሀኒት ጋር እንደ ሆርሞናል ቴራፒ መድሀኒት በጋራ መጠቀምን አፅድቋል ።

ይህ ጥምረት PIK3CA-mutated የሚባል የካንሰር ህዋስ ላለባቸው ታካሚዎች ህክምና ውጤታማነትን ይጨምራል ፡፡ FDA በተጨማሪም በደም እና በህብረ ህዋሳት ናሙና ላይ PIK3CA mutation ለመፈለግ companion diagnostic therascreen የሚባለውን ምርመራ አፅድቋል ይሄም ለህክምና ባለሙያዎች ለካንሰር ህክምና በትልቁ ይረዳቸዋል።

በMay 24 2019 በአለም ትልቁ የካንሰር ኮንፈረንስ በሆነው በAmerican Society of Clinical Oncology (ASCO) አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ እንደታወቀው alpelisib የተባለውን መድሀኒት ከfulvestrant ጋር አብሮ መጠቀም በጡት ካንሰር ታማሚዎች ላይ የካንሰር ህዋሳትን የመሰራጨት እድል ይቀንሳል fulvestrant እንኳ በራሱ progression free periodን በእጥፍ ያሳድገዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የribociclib መድሀኒትን ከሆርሞን ቴራፒ መድኃኒቶች ጋር አብሮ መጠቀምን የሚያበረታቱ የምርምር ውጤቶች ተገልፀዋል፡፡  የወር አበባቸው ሊቆም ለደረሱ ታማሚዎችና የተባባሰ ወይም የተሰራጨ የጡት ካንሰር ላለባቸው ታስቦ ribociclib ከሆርሞን ቴራፒ  ጋር ሲወዳደር የመዳን እድላቸውን 50% ያህክል  ይጨምራል። ይህም ከእንደዚህ ዓይነቱ ህክምና ተጠቃሚ ለመሆን የሚጠብቁትን ህመምተኞች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል ፣ ከዚህ ቀደም ግን የወር አበባቸው ለቆመ ታማሚዎች ብቻ ነበር የታሰበው።
 
ቢሆንም ግን FDA alpelisib የተባለው መድሀኒት እንደ Steven-Johnson syndrome ፣ Erythema multiforme (EM) ወይም Toxic Epidermal Necrolysis (TEN) አይነት ከባድ የቆዳ ችግር ለነበረባቸው ታማሚዎች ጥሩ እንዳልሆነ ያስጠነቅቃል።

የአሜሪካው FDA alpelisib ከ fulvestrant ጋር ለአገልግሎት እንዲውል መፍቀድ  እንዲሁም በወጣት ታማሚዎች የcompanion diagnostic therascreen ምርመራ በማድረግ የribociclib መድሀኒትን ከሆርሞን ቴራፒ ጋር እንዲሰጥ መፍቀዱም ጥሩ ዜና ነው።
የዚህ የሕክምና ሂደት ውጤታማነት መሠረት በሌሎች ሀገሮች ውስጥ ያሉት የጤና ባለሥልጣናት ይህንን የሕክምና ዕቅድ ወደፊት በቅርብ ጊዜ ሊጠቀሙ ይችላሉ ፡፡ አሁን በአለም ላይ ላሉ የጡት ካንሰር ታካሚዎች ረጅም እድሜ ለመኖር እና የተሻለ ጥራት ያለው ህይወት ለመኖር አዲስ ተስፋ አለ።
 
For more information please contact:
Last modify: ኖቬምበር 29, 2024

Related Packages

Related Health Blogs