‹‹ተስፋዬ፡ ሚስቴ ቀዶ ጥገናውን ትተርፋለች በሚል የሰነቅኩት ተስፋ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የነበረኝን ስሜት ለመግለፅ እጅግ ከብዶን ነበር፡፡ ሁላችንም ስለእጅግ መልካም ነገር ተስፋ እናደረጋለን፡፡›› ይህ ሰሚር ሻርም እጅግ ስለሚያፈቅራት ሚስቱ ህይወት የገለፃቸው ቃላት ናቸው፡፡
ሳሚር ሻርም ከአንድ ሀገር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቀጥረው በታይላንድ በዲፕሎማት ደረጃ እጅግ ከሚወዳት ባለቤቱ ሬኑ እና ከ15 ዓመት ልጃቸወው ጋር ላለፉት 12 ዓመታት በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡ በታይላንድ ኑሮአቸው በጭራሻ ያልታሰበ ዱብእዳ እስካጋጠማቸው ድረስ እጅግ አስደሳች ነበር፡፡ ‹‹በሕይወቴ ውስጥ እጅግ በጣም መጥፎ ነገር ያጋጠመኝ ከሶስት ዓመት በፊት በባለቤት ጡት ላይ ትንሽ እና በጣም ህመም የተሞላበት ምልክት በታየበት ጊዜ ነበር፡፡ በመሆኑም በቡምሩንግራድ ሆስፒታል እንድትመረመር ወስነን ወደ ሆስፒታል ባቀናንበት ወቅት በጡቷ ውስጥ 5.8 ሳ.ሜ ዕጢ እንደሚገኝበት በምርመራ አረጋገጡልን፡፡›› በዚህም ሳሚር ሻርማ እጅግ አስደንጋጭ ዜና እንደሰማች ተረዳ፡፡
በወቅቱ እሷ ተመርምራ ውጤት ሲነገራት እኔ ከታይላንድ ውጪ ነበርኩኝ፡፡ ከዚያን በኋላም የውጭ ጉዞዬን ጉዳይ እንዳጠናቀኩኝ ወዲያው እሷን ለማሳከም እንደቸኮለ ሰሚር ሻርማ ገልጿል፡፡ በመሆኑም ስለ ህክምናው ዝርዝር ሁኔታዎችን ወደ ማከናወን ገባሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንደታወቀ ህክምናውን ማፋጠን እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት የህክምናውን ሂደት መጀመር እንዳለንበት ተገንዝበዋል፡፡ ሐኪሞች የግራ ጡቷን ሙሉ በሙሉ በህክምና ማስወገድ ኖርባቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በጨረር የሚሰጥ ሕክምና ለ12 ጊዜ ታካሄዳለች፡፡››
ምንም እንኳ አንዳንድ ጎንዮሽ ችግሮች ቢኖሩትም የህክምናው ሂደት በአግባቡ እየሄደ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በቤተሰቦች በተሰጡት ተስፋ እና የሞራል ድጋፍ ሁሉም እንቅፋቶች መቋቋም ተችለዋል፡፡ ከዚያ በኋላም የህክምናው ማጠቃለያ ሂደት ወደመስጠት የተሸጋገረ ሲሆን ይህም በግምት ለአንድ ዓመት (ከ6-9 ወር) የሚሰጥ የኬሚካል ሕክምና ወይም የኬሞቴራፒ ሕክምና ነበር፡፡ ለካንሰር በሽታ ከሚሰጡ በርካታ ሕክምናዎችም የኬሞቴራፒ ወይም የኬሚካል በሽታ ከሚሰጡ በርካታ ሕክምናዎችም ኬሞቴራፒ ወይም ኬሚካል ሕክምና እጅግ ከባዱ ህክምና ክፍል ነው፡፡ የሚሰጣት ሕክምና በሰውነቷ ላይ የተፈለገውን ውጤት ሳያመጣ ሲቀር ባለቤቴ ወደ ድንገተኛ ሕክምና ክፍል በምትወሰድበት ጊዜ እጅግ እያዘነች ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች በአግባቡ ስለሄዱልን ሐኪሞች እና ነርሶች ላደረጉልን እንክብካቤ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበናል፡፡ በሂደትም የጡት ካንሰሯ ሙሉ በሙሉ ከውስጥዋ መወገዱን በተነገረን ወቅት ከፍተኛ ደስታ ተሰማን፡፡ ‹‹ለሁላችሁም እጅግ በጣም አድናቆቴን ሰጥቻለው፡፡›› ሰሚር ሻርማ በፈገግታ ነገረን፡፡
አሁንም ከቃላቶቹ ውጪ አይደለም
‹‹ሁሉም ነገር በአግባቡ እየሄደ መሰሏል፤ የቀድሞ የቤተሰባችን ደስታ ተመልሶልናል፡፡ ነገር ግን ከአንድ ዓመት በኋላ እኔ በቶንጋ ስራ ላይ እያለሁ በድጋሚ ሌሎች በርካታ የተደበላለቁ ዜናዎችን ሰማው፡፡ ሚስቴ ሬኑ እንደገና ከባድ ህመም በደረቷ ላይ ይሰማት ጀመር በጣም መጥፎ ነገር ነበር፡፡ በህመሙ ምክንያት ለመተንፈስ ያልቻለች በመሆኗ አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋት ነበር፡፡ በዚህ ምክንያትም እሷን ሆስፒታል ለህክምና ለመውሰድ በቶንጋ የነበረኝን ስራ አቆምኩኝ፡፡ ባለቤቱ ከካንሰር ሙሉ በሙሉ ነፃ እስከምትሆን ድረስ ለማሳከም እንደወሰነ ሰሚር ሻርማ ገልጿል፡፡ ከእኛ ጋር እድል የራሷን ድርሻ እንደምትጫወት በመረዳት ምክንያትም በወቅቱ ታክማ ከካንሰር ነፃ ሆኖ የነበረች ሚስቴ በድጋሚ በካንሰር መያዟ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ወደ ሳንባዋ ሊዛመት ይችላል፡፡ በጣም ከብዷታል›› በማለት ሰሚር ተናግሯል፡፡
‹‹ለሕክምና በድጋሚ ስንሄድ ዶክተር ሱቲዳ ሱዋንቬቶ ያገኘን ሲሆን እሳቸውም ከፍተኛ የአንኮሎጂነስት ባለሙያ ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ዶክተሯ ልበሙሉም ነች፡፡ በዚህም የተነሳ የካንሰር በሽታ በቀላሉ በሕክምና የማይድን ነው የሚለውን አስተሳሰባችን በቀላሉ አስወገደችልን፡፡›› በማለት ሰሚር ተናግሯል፡፡ የኬሚካል ሕክምና ወይም ኬሜቴራፒ ሕክምና ቀላል ሂደት አይደለም፡፡ ሐኪሞቹ ሕክምናውን ለማቆም የተገደዱ ቢሆንም ግን ጤናዋ እንዲሻል ቤተሰቦቿ እና የህክምና ቡድኑ ከፍተኛ እንክብካቤ አድርገዋል፡፡ በሕክምናዋ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት ከባድ ፈተና አጋጥሞናል፡፡
በሕክምናው ሂደት ወቅት ያጋጠሙ ውስብስብ ሁኔታዎች ስላታወቀ ሁኔታዋ በእያንዳንዱ ሂደት የቅርብ ክትትል አስፈልጓት ነበር፡፡ እጅግ በከባድ ሁኔታ ያስመልሳት ነበር፤ በጀርባ አጥንቷም ከባድ ህመም ይሰማት ነበር፡፡ በአጠቃላይ በከባድ ህመም ትሰቃይ ነበር፡፡ እኔንም በተመሳሳይ መልኩ ጎድቶኛል፡፡ ከዚያን በኋላ ቀዶ ጥገና ህክምና እንዲደረግላት ዶክተር ሱቲዲ ወሰነች፡፡ የቀዶ ጥገናውን ሕክምና በማቆየት ስለቅድመ ቀዶ ጥገና ምርመራዎች ዝርዝር ሲደረጉላት ሁኔታዎቹ እጅግ ተወሳሰቡ፡፡
‹‹ከዚያን በኋላ የእሷ ጉዳይ በሙሉ በባለሙያዎች እጅ እንደሆነ አረጋገጥኩ፡፡ ምንም ማድረግ ባንችልም ለቡድኑ በሙሉ ምስጋናችን አቅርበናል፡፡ ምስጋናችን ከሐኪሞቹ ጀምሮ እስከ የመድሃኒት ባለሙያዎች በቡድኑ ለነበሩ ይገባቸዋል፡፡ በእነዚህም ጊዜ ሁሉ እኔም ህክምና መከታተል ነበረብኝ፡፡ ይሁን እንጂ በየጊዜው ከሁሉም የቡድኑ አባላት በቂ እና ጠቃሚ ምክሮች እየተሰጡኝ ነበር፡፡›› ይላል ሰሚር፡፡ የምርመራው ውጤት እንደደረሰም ሚስቱ በጣም ተዳክማ ስለነበረች ቀዶ ጥገና ሕክምናውን ማስተላለፍ እንደነበረበት ሲናገር የቀረው የመትረፍ እድል 10 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ ዶክተሩ ሱቲዳ ለእኔ በጣም ግልፅ ነበሩ፡፡ በመሆኑም ሰውነታቸው እንደዚህ ዓይነት የተዳከሙ ህሙማን ቀዶ ጥገና ውጤት ስኬታማ ይሆናል ብሎ ማሰብ እጅግ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ዶክተሯ ነገሩኝ፡፡ በመሆኑም የቀዶ ጥገና ህክምና ከተደረገለት የባለቤቴ መትረፍ እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ ባይደረግ እንደሚሻል ዶክተሯ ነገሩኝ፡፡
ከቅሬታ በላይ ጥንካሬ መጎናፀፍ
‹‹ሬኑ ማለት ለእኔ መላው ዓለሜ ማለት ነች፡፡ ምንም ቢያጋጥማት እስከ መጨረሻ ሰኮንድ ድረስ ከጎኗ እሆናለሁ፡፡ በማንኛውም ረገድ እሷ የምትፈልጋቸውን ሁሉ አሟላላታለሁ፡፡ ሐኪሞቹም በሚገርም ሁኔታ ሁልጊዜም ከጎናችን በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ እያደረጉልን መንፈሳችን ያድሳሉ፡፡ በትኩረት የመስመጥ ፀሎት እንድናደርግ ያስተምሩን ነበር፤ መልካም አስተያየቶችን ይሰጡን ነበር፡፡ እኔ ባየሁት መሰረት ለ25 ዓመታት በትዳር የቆየንበት ዘመን ሁሉ በደስታ አብረን የትዳር ሕይወት ያለሳለፍን የነበርን ቢሆንም ግን ለ25 ወራት እሷ በካንሰር ተይዛ ያሳላፍነው ጊዜ ከምንም በላይ በጣም ከባድ ጊዜ ያሳለፍንበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡››
ለሌሎች የሚለገሱ የማበረታቻ ቃላት
‹‹ሆስፒታሉ እጅግ በጣም የምንወዳቸው ታካሚ ወዳጆቻችን በተፈለገው ሁኔታ ታክመውበት ሚፈወሱበት ብቻ ሳይሆን ለእኛ ለአስታማሚዎችም እጅግ በጣም መልካም ሆስፒታል መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ ይገባናል፡፡ መልካም እና የተመሰገኑ ሆስፒታሎች ታካሚዎች ያለተገቢ ዋጋ ከእነሱ ዘንድ እንዲቆዩ አያደርጉም፡ በዚህ ሆስፒታል የሚገኙ ሰዎች በሙሉ ምንግዜም ከአጠገባችን መሆናቸው ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ተስፋ እንድንቆርጥ አያደርጉም፡፡ በዚህም ረገድ ግንባር ቀደም ስመ ጥር ሆስፒታል ሆራይዘን የካንሰር ህክምና ማእከል ሆስፒታል አንደኛው እና ዋነኛው ነው፡፡ በእኛ ሁኔታ ረገድ ሆስፒታሉ ለታካሚያችን እና ለመላው ቤተሰቦቻችን መልካም ፈውስ ሰጥተውናል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አይነቱ ደስታ ማጎናፀፍ የሚቻለው ታካሚ ቤተሰብ አባላት እና የህክምና ባለሙያ ቡድን በጋራ ተናብበው እና ተገናዝበው የጋራ ትብብር እና ቅንጅት ከፈጠሩ ብቻ ወይም መፍጠር ከቻሉ ብቻ በትክክል የሚሳካ ሆናል፡፡ እባክዎ እንዳያቋርጡ፤ እጅ እንዳሰጡ! በዚህ መንገድ መታገል ይቀጥሉ ! ሐኪሞች ለሁላቸውም ተመሳሳይ በሆነ አካሄድ የቻሉትን ሁሉ የሚሰሩ መሆናቸውን እምነታቸውን ጣሉባቸው፡፡ ምንም እንኳ ከፊት ለፊታችን የሚጠብቀን ጉዞ ቀላል ባይሆንም ግን፤ ሁላችንም እረስ በርሳችን ተማምነን ከሄክድንበት መቋቋም እንችላለን፡፡›› በማለት ሰሚር በሙሉ ተስፋ ይገልፃል፡፡
For more information please contact:
Last modify: February 11, 2021