በሮቦት የታገዘ የዳቬንቺ ቀዶ ጥገና አገልግሎት (Prostatectomy) በጣም ዝቅተኛ የምርመራ ተጋላጭነት እና አማራጭ ያለው ነው፡፡ በከፍተኛ እና በላቀ ቴክኖሎጂ ግኝት መሰረት ውጤት በሆነው ካሜራዎች በከፍተኛ ደረጃ አቅርቦ የማሳየት አቅም ያለው ካሜራ በመጠቀም ለህክምና ሚስፈልገው እና ለቀዶ ጥገና ዶክተሩ አመቺ በሆነ ሁኔታ እንዲታይ ለማድርግ ይረዳል፡፡ የሮቦት ክንድ አካል ወገብ ወይም እንቅስቃሴ በተለይ ከሰው እንቅስቃሴ ጋር በቴያዘ ለቀዶ ጥገና ባለሙያዎች ተገቢ እና ትክክለኛ ቦታ ለይቶ ለማሳየት ይረዳል፡፡ ሌላው በተመሳሳይ መልኩ እኩል የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው brachytherapy, የሚባለው የህክምና አገልግሎት ሲሆን ይህም የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው የጨረራ አመንጪ ነገሮችን በካንሰር በቀጥታ የተጠቃው አካል ላይ በመትከል የሚሰጥ የህክምና አይነት ነው፡፡ በካንሰር የተጠቃው የአካላችን ክፍል በቀጥታ ከዚህ አይነት የህክምና ምንጭ በከፍተኛ የህክምና ጨረራ የሚያገኝ ሲሆን የጨጨራውን መጠን በመቀነስ ወደ አካባቢው የሰውነታችን ክፍሎች ዙሪያ ማሰራጨት ይቻላል፡፡
የፕሮስቴት ግላንድ ወይም የዘር ፍሬ እጢ መሰረታዊ የወንዴ መራቢያ አካል ነው፡፡ በማንኛውም የሰው ልጅ እድሜ በማንኛው ጊዜ እድገቱን የማያቆም የሰውነታችን ክፍል በመሆኑ ከሌሎች የተለየ የሚያደረግው ይህ አይነት እድገት የማያቋጥ አካል በመሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የፕሮስቴት ወይም የወንዴ መራቢያ እጢ የሆነው ከመጠን በላይ በሚያድግበት ጊዜ ለበርካታ ችግሮች ሊጋለጥ ይችላል፡፡ በቀላሉ የወንድ መራቢያ ክፍል (
benign prostate hyperplasia), ምልክቶች በተለይ በሽንት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት ወይም ውሃ ሽንት መምጣት ተገቢ እና የዚህ በሽታ ወይም የእጢ እድገት ወይም ከመጠን በላይ ማደግን ያመለክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ የዘር ፍሬ ክፍል የሚያጠቃው ካንሰር በወንዶች ላይ ከሚከሰተው የካንሰር በሽታ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ለህክምና አስቸጋሪ የሆነ የካንሰር በሽታ ነው፡፡
የጥናት እና ምርምር መረጃዎች እንደሚያሳዩት የዘር ፍሬ የሚያጠቃው ካንሰር በሽታ የሚታወቀው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ነው ይህ ደግሞ ለበሽው የሚደረገውን ህክምና አሰጣጥ ያወሳስባል፡፡
በአፋጣኝ ምርመራ በማድረግ በሽታውን ለይቶ ማወቅ ለውጤታማ እና ስኬታማ እቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ የአሜሪካ የካንሰር በሽታ ማህበረሰብ በተወሰነ እድሜ ክልል ውጥ የሚገኙ ወንዶች የPSA ደረጃ ምርመራ በየአመቱ በደም ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ፡፡ ስለPSA የምርመራ መሳሪያ እና ስል
PSA የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጠን በሆራይዘን የካንሰር ህክምና ማዕከል ዩሮሰርጀን የሆነውን ዶ/ር ቻሩስፖንግ ዲሳራናን አናግረነዋል፡፡
የ PSA ምርመራ አላማ ምንድነው እና ውጤቶቹስ ምን ማለት ናቸው?
ዶ/ር ቻሩስፖንግ፡- የPSA ምርመራን የምንጠቀመው የዘር ፍሬ ካንሰር መኖሩን ሊያሳየን የሚችልን ፕሮቲን ቼክ ለማድረግ
ነው፡፡ የፕሮስቴት ካንሰር ወይም የወንዴ መራቢያ ክፍል የሚያጠቃ ካንሰር ገና ሲጀምር ምንም አይነት ምልክቶች አያሳይም ነገር ግን የ PSA ደረጃን ከፍ ያደርጋል፡፡ PSA የምርመራ አገልግሎት የፕሮስቴት ካንሰር ወይም የወንዴ መራቢያ ክፍል የሚያጠቃ ካንሰር ለመለየት የሚያገለግል ጠቃሚ የምርመራ ስልት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የ PSA ደረጃ ብቻውን የዚህ አይነት ካንሰር መኖሩን ላያረጋግጥ ይችላል፡፡
ወንዶች በየስንት ጊዜ የ PSA ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል?
ዶ/ር ቻሩስፖንግ፡-
እድሜያቸው ከ50 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች በየአመቱ 1 ጊዜ የዚህ አይነት የካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡ በዚህ ምርመራ ውጤት መሰረትም የተፈለገው የበሽታው ማመላከቻ መሳሪያ ከመደበኛ መጠኑ ውጪ ከወጣ ለዶ/ር ውጤቱን በማሳየት በየ 6 ወር ተገቢ ምርመራ በማድረግ ካንሰሩን ከስሩ ለመቆጣጠር ይቻላል፡፡
የ PSA ደረጃ ውጤት ከፍተኛ ከሆነ በቀጣይ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?
ዶ/ር ቻሩስፖንግ፡- የምርመራው ውጤት በ2 ሰዓት ውስጥ ይገኛል፡፡ የ PSA ምርመራ ደረጃ ከፍተኛ ከሆነ የMRI, ምርመራ እንዲያደርጉ እመክራለሁ፡፡ በዚህም የፕሮስቴት ወይም የወንዴ መራቢያ ክፍል እና ዙሪያውን ገፅታ በመውሰድ እስካን በማድረግ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ የMRI, ምርመራ ውጤት ጤናማ ያለመሆኑን የሚያረጋግጥ ከሆነ በቀጣይ መወሰድ ያለበት ምርመራ የMRI, አልትራ ሳውንድ ምርመራ ባይፖሲ በማድረግ እና በዚህ መሰረትም ናሙናው ተወስዶ የካንሰር ህዋሳት መኖራቸውን መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ምርመራ ውጤቱ ላይ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ ጥያቄ የህክምናው ጉዳይ ይሆናል፡፡ የህክምና ምርመራ አማራጮች ብዙ ጊዜ የጨረራ ህክምና/ራዲዮቴራፒ የኬሚካል ህክምና/ኬሞትራፒ ወይም የሆርሞን ቴራፒ ህክምና ማድረግን የሚያካትት ሲሆን የእነዚህ ህክምና አሰጣጥም የካንሰሩ ህዋሳት የሚገኝበት ደረጃ መሰረት የሚሰጡ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ የፕሮስቴት ግላንድ ወይም ወንዴ መራቢያ አካልን በቀዶ ጥገና ማውጣት( prostatectomy) ለዚህ የካንሰር አይነት ዋነኛ ህክምና ነው፡፡ በጣም የሚመረጠው የቀዶ ጥገና መንገድ laparoscopic radical prostatectomy የሚባለው ነው፡፡ በዚህ መንገድ ዶክተሩ ትንሽ ካሜራ በረጅም ቀጭን ቱቦ ያሰገባና በመቆጣጠሪያው እየተከታተለ ቀዶ ጥገናውን ያካሂዳል፡፡ ታካሚውም ከዚህ ቀዶ ጥገና እስከሚያገግም ድረስ እስከ ሶስት ቀን ሆስፒታል ይቆያል፡፡
ነገር ግን አዲስና እና ከዛም የተሻለ ውጤታማ የሆኑ የቀዶ ጥገና መንገዶች በአሁኑ ጊዜ በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛል፡፡ Robotic–assisted da Vinci Surgery or Da Vinci® Prostatectomy ህክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ዶ/ር ቴራፖን አሞርንቨሱኪት በበምሩንግራድ አለም አቀፍ ሆስፒታል በዩሮሰርጀን የህክምና ዘርፍ በርካታ የስራ ልምድ ያለው ሲሆን በተለይ ከዚህ አይነት የካንሰር በሽታ ጋር ተያይዞ ለበርካታ አመታት ለህሙማን ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ በመሆኑ በዚሁ በ3ዲ ገፅታ የቀዶ ጥገና መስራት ለቀዶ ጥገና ዶክተሮች በሌሎች በክፍት ወይም መደበኛ keyhole (non-robotic) laparoscopic ቀዶ ጥገና ከመስራት በጣም በተሻለ እና ግልፅ ስርአት ተከትሎ ተገቢ እና ትክክለኝ ህክምና አገልግሎት በማእከሉ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ከፍተኛ ጥራት ባላቸው መነፅሮች በመታገዝ ህክምና የሚሰጥበት የሰውነት ክፍል ለቀዶ ጠገና ዶክተሩ በጣም ግልፅ በሆነ እና በቅርብ እይታ ይታየዋል፡፡ ትንንሽ የቀዶ ጥገና መሳሪያዎችን የሚይዙት የሮቦት እጆች የዶከተሩን የእጅና የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴዎቸነ ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ እየተቀበሉ ቀዶ ጥገና ዶክተሩ ትክክለኛና ውጤታማ ኦፕሬሽን እንዲያደርግ ይረዱታል፡፡ ይህ አይነቱ የህክምና አገልግሎት እንደ laparoscopic ቀዶ ጥገና ዝቅተኛ ህመም የሚያስከትል እና በፍጥነት ከቁስሉ ለመዳን ጥሩ መሆን ብቻ ሳይሆን የሽንት ፍሰትና የብልት ያለመቆም ችግሮችንም ይቀንሳል፡፡
ሌላው ተመሳሳይ ተፈላጊነት ያለው የህክምና አገልግሎት (brachytherapy,) ሲሆን በዚህ አይነት የህክምና አገልግሎትም በካንሰር የተጠቃው የሰውነት አካል ላይ በቀጥታ ቀጭን ቱቦ በመጠቀም ጨረር መልቀቅን የሚያካትት ሲሆን በዚህ ወቅት በካንሰር የተጠቃ የሰውነት ክፍልም በቀጥታ ከጨረራ አመንጪው ቁስ ከፍተኛ መጠን ያለው ጨረር በመቀበል በአካባቢው የሰውነት ክፍል ላይ ግን እንዲቀነስ ይደረጋል፡፡ ዶ/ር ኢፒቻርት ፓኒቸቫሉክ የራዲዮሎጂስት ባለሙያ ሲሆን በካንሰር ህክምና ሆሪዞን ማእከል ከዚህ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡
በ“
In high dose rate (HDR) brachytherapy, ቀጭነ ቱቦ ወደ ዘር ፍሬ Transrectal Ultrasound Guidance (TRUS) በመጠቀም ቀድሞ የተሰላውን የጨረር ህክምና ወደ ካንሰር ህዋሱ እንለቃለን፡፡ ይህመ ካለቀ በሁዋላ የተጠቀምንባቸው መሳሪያዎች ይወገዳሉ ምንም ነገር ሳይቀር፡፡
የዚህ የህክምና አገልግሎት ዋና ጥቅሙ ለህክምና አገልግሎት የሚለቀቀው ጨጨር መጠን አሁንም በታማማው ታካሚ ውስጥ ቀጭኗ ቱቦ እያለች በተከታታይ የሚስተካከል ይሆናል፡፡ የHDR ህክምና አገልግሎት በጣም ውጤታማ ሲሆን ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የዚህ አይነት የካንሰር በሽታ ለማከም የሚረዳ ሲሆን ከ90% በላይ ህክምና ስኬት ይሰጣል፡፡ የዚህ አይነቱ የህክምና አገልግሎት የጎንዮሽ ጉዳት ከሌሎች የህክምና ስርአቶች ጋር ሲነፃፀርም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ዝቅተኛ ስጋት ላለው እና የተወሰነ ቦታ ላይ ለሆነ የዘር ፍሬ ካንሰር permanent implantation የተሻለ የbrachytherapy አማራጭ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የጨረራ ምንጭ ከተጠቃው አካል ጋር እስከ መጨረሻው የሚተከል ይሆናል፡፡ የጨረራ ምንጩ የሰሊጥ ፍሬ ከሚያክል የሚመነጭ ሲሆን ቀስ በቀስ በጣም ዝቅተኛ መጠን ያለው ጨረር እየለቀቀ የሚያፀዳ ይሆናል፡፡
የጨረራ ምንጩ በቀጥታ በካንሰር ህዋሳት የተጠቃው አካል ውስጥ በቋሚነት የሚገጠም ሲሆን የሚለቀቀው የጨረር መጠን በተገቢው ሁኔታ ተሰልቶ መጠኑ የተፈለገውን ያህል ብቻ መሆን ይገባዋል፡፡
አሁንም ገና ብዙ አማራጭ አለ።
በምስል የተደገፈ ራዲዮቴራፒ (IGRT) ማለትም የተሻሻለው የባህል ውጫዊ ጨረር ስሪት ህክምና፡ ዝቅተኛ ተጋላጭነት ያላቸው የፕሮስቴት ካንሰር ህመምተኞችን ከ90 ከመቶው በላይ የመፈወስ ደረጃ ሊሰጣቸው ይችላል ፡፡ በመጀመሪያ ፣ የወርቅ ሰራሽ አመላካቾች — ሦስት ጥቃቅን የንፁህ ወርቅ ቅንጣቶች ወደ ፕሮስቴት(የዘር ፍሬ) ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል። ከዚያ በኋላ ታካሚው የCT-scan ምርመራም ማከናወን በሚችል ማሽን አንድ የጨረር መጠን ይሰጠዋል፡፡ ሦስቱ ጥቅጥቅ ያሉ የወርቅ ቅንጣቶች በስዕሉ ላይ ይታያሉ ፣ ይህም ሐኪሙ የካንሰር ዕጢውን በትክክል እንዲያነጣጥር ይረዳዋል፡፡ ይህ በአካባቢው ያሉ ጤናማ ሕብረ ሕዋሳት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ይቀንሳል እንዲሁም ከቀድሞ የሕክምና ዘዴዎች ጋር ሲነፃፀር ሕክምናው የሚወስደውን ጉዞ በአጭሩ ያሳጥረዋል፡፡
በሆሪዞን የካንሰር ህክምና ማእከል የሚገኙ ሀኪሞች በካንሰር የተጠቃው የሰውነት ክፍል ወይም ህዋስ መጠን፣ የሚገኝበት የአካል ክፍል እና የበሽታው ደረጃ መለየትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰሩ ሲሆን አላማውም ተገቢ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ስለ ካንሰር በሽታ መረጃ መኖር እና ተገቢ ግንዛቤ መያዝ እንዲሁም በየጊዜው የጤና ምረመራ ማድረግ ለማንኛውም ነገር ዝግጁ እንድንሆን ይረዳናል፡፡
በዛሬ ጊዜ በካንሰር በሽታ ላይ ስፔሻላዝድ ያደረጉ ዶክተሮች አቅም እና ክህሎት ከወቅቱ የላቀ ህክምና ቴክኖሎጂ ጋር በመሆን የዘር ፍሬ ካንሰር ህክምና በፊት ከነበረው የተሻለ ህክምና እንዲሰጥና አስፈሪነቱም ያነሰ እንዲሆን ለማድረግ አስችሏል፡፡
For more information please contact: