ለታካሚው በጣም ጥሩውን አቀራረብ መፈለግ ፡፡
አንድ ታካሚ የረጅም ጊዜ የጨረር ሕክምና አደረገ ማለት በታካሚው ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ አነስተኛ ይሆናል ማለት ነው ፡፡ የሕክምናው ርዝመት የሚወሰነው በካንሰሩ ዓይነት ነው ፡፡ በBumrungrad International Hospital የሆራይዘን ካንሰር ህክምና ማእከል የጨረር ኦንኮሎጂስት እና የሬዲዮሎጂ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሱናታን እንደነገሩን “የጨረራ ሕክምና ምንም አያምም ኤክስ ሬይ ከማድረግ የተለየ አይደለም፡፡ የህክምናው ቆይታ በታካሚው ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ይለያያል። የፕሮስቴት ካንሰር ስምንት ሳምንታት ሊወስድበት ይችላል ፣ የጡት ካንሰር ግን ስድስት ሳምንቶች ፣ እንዲሁም የሳንባ ካንሰር ከስድስት እስከ ሰባት ሳምንታት ሊወስድ ይችላል፡፡ የታካሚው ጤናማ ሕዋሳት በጨረሩ ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማረጋገጥ የጨረር ሕክምና በረጅም ጊዜ ውስጥ እያለፈ እያለፈ ሊሰጥ ይችላል። “
ዶክተር ሱንታና አክለውም ”አንዳንድ ጊዜ ታካሚዎች ይሄኛውን ህክምና ቶሎ ለመጨረስ ስለሚፈልጉ፡ ከፍ ያለ የጨረር መጠን እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ነገር ግን እንደዛ ማድረግ አንችልም፡፡ ከህክምናው በኋላ የሚኖረውን የታካሚውን የህይወት ጥራት ከግምት ማስገባት አለብን ፡፡
ታካሚዎቻችን ምን እንደሚጠብቁ እንዲያውቁ ከህክምናው በፊት በህክምናው ሊኖሩ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሁልጊዜ ለታካሚዎቻችን እንመክራለን ፡፡ በአፍ ወይም በአንገት ላይ ህመም፣ የአፍ መድረቅ፣ የመዋጥ ችግር ወይም ክብደት መቀነስ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ዶክተሩ እነዚህን የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዴት መቀነስ እንደሚቻል ወይም ታካሚው የምግብ ባለሙያ እንዲያናግሩ ይመክራል ፡፡ ”
የጨረራ ሕክምና በሰውነት ውስጥ ባሉት የካንሰር ሕዋሳት ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ኃይል ያለው ጨረር ይጠቀማል። በሆራይዘን ካንሰር ህክምና ማእከል ለ23 ዓመታት የቆዩት ዶ/ር ሱንታና የአሰራር ሂደታቸውን አስረድተዋል፡፡ ታካሚዎቼን ቃለ መጠይቅ በማድረግና እና ታሪካቸውን በመውሰድ እጀምራለሁ፡፡ ለምሳሌ ፣ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎችን የትንፋሽ እጥረት ወይም ሳል እያሳዩ እንደሆነ እንዲሁም ትኩሳት እንዳላቸው እጠይቃለሁ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ምልክቶች የተገናኙ ስለሆኑ ወደ ኢንፌክሽን ወይም ወደ መቆጣት ሊያመራ ይችላል።
በተጨማሪም ፣ ዕጢው ያለበት ቦታ እና መጠን በትክክል ማወቅ እንዲሁም የደም መፍሰስ መኖር አለመኖሩን ማወቅ አለብን። ለምሳሌ ፣ አብዛኛዎቹ የጡት ካንሰር ህመምተኞች በሕክምናቸው ወቅት የጡት ጥበቃን ይመርጣሉ፡፡ ይህ አካሄድ ስኬታማ እንዲሆን ዕጢውን እና ንፍፊቶችን ማስወገድ ከዛም የጨረር ሕክምና መሰጠት አለበት፡፡ እኛም የካንሰሩን ደረጃ ማወቅ እና ሌሎች ሊከሰቱ ለሚችሉ ማናቸውም ችግሮች ቅድመ ሁኔታዎችን እና ህክምናዎችን ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆን አለብን ፡፡
ከህክምናው በላይ የሆነ እንክብካቤ ፡
ዶክተር ሱንታና የካንሰር ምርመራ እና የጨረር ሕክምና ጥልቅ ልምድ ያላቸው ባለሙያ እንደመሆናቸው መጠን የተሻለው አቀራረብ ከታካሚው ጋር በመተማመን እና በጎ ፈቃደኝነትን በመገንባት ላይ መሆኑን ተገንዝባለች ፡፡ ብዙውን ጊዜ የሕክምና ኦንኮሎጂስቶችን እየጋበዝኩ በበሽተኛው ፊት ከእኔ ጋር የታካሚውን የምርመራ ፊልሞች አብረውኝ እንዲመረምሩ እጋብዛለሁ። በታማሚው ሙሉ ተሳትፎ እና እንዲሁም ታማሚው ጥያቄዎችን በነፃነት እንዲጠይቅ በመጠየቅ የሕመምተኛውን ሁኔታ በይፋ እንወያይበታለን እንዲሁም ምርመራ እናደርጋለን እንዲሁም የማመዛዘን ሂደታችንን ይመለከታል። ይሄም የታካሚውን ፍርሀትና ጭንቀት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
ዶክተር Sunantha ሕመምተኞች ስለ ጨረር ሕክምና ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥማቸውን አንዳንድ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ጠቅሰዋል ፡፡ አንዳንዶቹ የጨረር ሕክምና ከኑክሌር ፍንዳታ አንድ ዓይነት ነገር ነው ብለው ያምናሉ” ዶክተር Sunthana ከሳቁ በኋላ ቀጥለውም ““ትልቅ ፍንዳታ ሊኖር እንደሚችል እና በጣም ሊጎዳ እንደሚችል ይሰማቸው ነበር። በጭራሽ እንደዚህ አይደለም! ለታካሚው የነገርኳቸውን ነገሮች ለማስታወስ እንዲረዱ ብዙውን ጊዜ ዘመዶቻቸውን በሕክምና እቅድ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እጋብዛቸዋለሁ ፡፡ ሕመምተኞች በብዙ ነገር ውስጥ እያለፉ ስለሆነ ሁሉንም ዝርዝሮች ለማስታወስ ይከብዳቸዋል፡፡ ዶክተር Sunthana ደግሞ ህመምተኞቻቸውን ስለ ስሜታቸው ዘወትር በመጠየቅ ፣ ጭንቀታቸውን ለመስማት እና እራሳቸው በእነሱ ላይ ምን እንደሚከሰት ጠንቅቀው እንዲያውቁ ታረጋግጣለች፡፡
“ይሄ ለእነሱ ትኩረት እንደምንሰጥና እንደምንጨነቅ ለእነሱ የምነግርበት የእኔ መንገድ ነው፡፡”
ከካንሰር ከትንሽ የጎንዮሽ ጉዳት ጋር ብቻ መዳን
ጥሩ የካንሰር ህክምና ቴክኖሎጂን ጨምሮ አንድ ላይ የሚመጡ ብዙ ነገሮችን ያካትታል፡፡ ለምሳሌ፣ ዕጢው ብዙውን ጊዜ መደበኛ ያልሆነ ስፋት ስላለው VMAT መጠቀም ከጨረር መጠን ጋረ በጣመ ትክክለኛ እንድንሆን ያስችለናል፡፡ ማሽኑ በሽተኛውን ይከብና የካንሰር ህዋስ በሚያገኝበት ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው ጨረር ይለቃል፡፡ ለሌሎች አካባቢዎች ጨረሩ በከፍተኛ ሁኔታ ያነሰ ይሆናል ፡፡ ይህ የፀሐይ ጨረር አጠቃላይ መጠን በትንሹ እንዲቆይ ያደርገዋል። ”
የታካሚው የአእምሮ ሁኔታ ወሳኝ ቁልፍ ነው፡፡ ለተሳካ ህክምና ውጥረትን እና ጭንቀትን መቀነስና መቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ የቡምሩንግራድ ሆስፒታል ሰራተኞች በየትኛውም ሥፍራ እጅግ በጣም ጥሩ የጤና ባለሙያዎች ናቸው፡፡ በሆሪዞን ህክምና ማዕከል ታካሚዎች ከጎናቸው አሸናፊ ቡድን እንዳላቸው እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡
ይሄም የረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሱንታና ሲሩሱቡት ፕሎይሶንግሳንግ የካንሰር ህክምና መርሆ ነው፡፡ ህክምናዎች በታካሚዎች ህይወት ላይ የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ እና በተቻለ ፍጥነት ወደ ጥሩ ጥራት ያለው ህይወት እንዲመለሱ ማድረግ ነው፡፡
For more information please contact:
Last modify: ኖቬምበር 30, 2024