bih.button.backtotop.text

የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና: ለሳንባ ካንሰር ሕክምና አዲስ ተጓዳኝ

ለረጅም ጊዜ የካንሰር ምርመራን ለማረጋገጥ የሚያገለግለው መንገድ ለምርመራ ከተጎዳው አካባቢ ህዋስ ቁርጥራጮችን መቁረጥና መመርመር    ይህ ብዙውን ጊዜ ለሳንባ ካንሰር ጉዳዮች የመረበሽ ምንጭ ነው ፣ ሳንባዎች እራሳቸው በቀዶ ጥገና ብቻ ለማግኘት ከባድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የሳንባ ካንሰር ህመምተኞችም በዕድሜ የገፉ ይሆናሉ ፣ ይህም ከቀዶ ጥገና የሚከሰተውን አደጋ ከፍ ያደርገዋል ፡፡ ፈሳሽ ባዮፕሲ ፣ እጅግ በጣም ቀላል የሆነው የምርመራ አቀራረብ 10 ሚሊ ሊትር ደም ብቻ ነው የሚጠይቀው። የዚህ ዘዴ ፍጥነት ፣ ትክክለኛነት እና ምቾት ወደ ቀጣዩ የህክምና ደረጃ ወቅታዊ እርምጃ እንዲኖር ያስችላል ፡፡

ለረጅም ጊዜ የካንሰር ምርመራን ለማረጋገጥ የሚያገለግለው መንገድ ለምርመራ ከተጎዳው አካባቢ ህዋስ ቁርጥራጮችን መቁረጥና መመርመር    ይሄም የtissue biopsy ወይም የህዋስ ባዮፕሲ በመባል ይታወቃል፡፡  በተለይ በአንዳንድ የሳንባ ካንሰር ዓይነቶች ፣ ኤክስሬይ ወይም ኤምአርአይ ምርመራዎች ለትክክለኛ ምርመራ በቂ ቢሆኑም እንኳን ፣ ሐኪሞች በጣም የተሻለውን የህክምና መንገድ ለመወሰን የበለጠ ዝርዝር መረጃ ይፈልጋሉ፡፡

ይህ ብዙውን ጊዜ ዶክተሮችን ለመወሰን የሚያስቸግር ነገር ነው ምክኛቱም እየታመመ ባለ የታካሚው ሰውነት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሂደት በባዮፕሲ ለማድረግ መወሰን ተጨማሪ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል፡፡   በተለይም ለሳንባ ካንሰር ህመምተኞች እውነት ነው ሳንባዎች እራሳቸው በቀዶ ጥገና ለማግኘት ከባድ መሆናጨው ብቻ ሳይሆን የሳንባ ካንሰር ህመምተኞችም በዕድሜ የገፉ ይሆናሉ ፣ ይህም ቀዶ ጥገናው የሚኖሩትን አደጋ ከፍ ያደርገዋል፡፡ የባዮፕሲ ምርመራው ራሱ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እና አጠቃላይ ህክምናውን ራሱ ረዘም ላለ ጊዜ ሊጎትት ይችላል። እነዚህ ተግዳሮቶች ናቸውየህክምና ሰራተኞች  በሕዋሳት ውስጥ ካንሰር መያዙን የሚያረጋግጡ አዳዲስ መንገዶችን እንዲፈልጉ ያነሳሳቸው፤ ስኬታቸውም የፈሳሽ ባዮፕሲ/ liquid biopsy/ ይባላል፡፡
 

ፈሳሽ ባዮፕሲ /Liquid Biopsy/ ምንድነው?

ለላቦራቶሪ ምርመራ ከታካሚው 10 ሚሊ ሊትር ያህል የደም ናሙና መውሰድን ያመለክታል ፡፡ ሆኖም የደም ናሙናው የካንሰር ሕዋሳት በደም ውስጥ መኖራቸውን ለመመርመር አይደለም ፣ ይልቁንም በደም ስሮች የሚሰራጩትን የካንሰር ሕዋሳት ዲ ኤን ኤ ለመመርመር ነው። ይሄ ዲ ኤን ኤ ከሌሎቹ ደህና ከሆኑት ህዋሳቶች ዲ ኤን ኤ እንዲለይ ሆኖ ይቀየራል፡፡ ናሙናው በጣም ትንሽ ከሆኑ ናሙናዎች ከፍተኛ ልዩ በሆኑ መሳሪያዎች ከመመርመሩ በፊት በመፅዳት ሂደት ማለፍ አለበት፡፡ የዚህ ዘዴ ፍጥነት ወደሚቀጥለው የህክምና ደረጃ ወቅታዊ እድገት እንዲኖር ያስችላል ፡፡

ይህ አይነት የምርመራ ዘዴ የሳንባ ካንሰር ህመምን non-small cell lung cancer [NSCLC]) ከማከም አንፃር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ለዚህ ምክንያት የሆነው ቀጥታ የካንሰሩ ህዋስ ላይ ኢላማ ያደረገ ህክምና ለማድረግ  የጎንዮሽ ጉዳቱ ትንሽ ስለሆነ ነው፡፡ የዚህ የመርመራ ሂደት ባህሪ የህክምና ባለሙያዎች ትክክለኛ የሆነውን የካንሰር ህዋስ የመለየት አቅም ሊኖር እንደሚገባና በዚህም የሚፈለገውን ወይም ኝ የተደረገውን ህዋስ ለመምረጥ እና ለማከም እጅጉን ይረዳል፡፡  
 
እ ኤ አ በ2019 በተካሄደው የEuropean Society for Medical Oncology (ESMO) ባደረጉት ስብሰባ በተደረጉት የተለያዩ ምርምርና ጥናቶች መሰረት የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና BFAST ጥናት ላይ ላቅ ያለ ጥቅም አለው፤ ይህም BFAST ሀመምተኞችን ለመለየትና ALK የህዋስ ልውጠትን በተመሳሳይ ለኬት በማወቅ ቀድሞ ከነበረው የፈሳሽ ናሙና በመውሰድ ለታካሚዎች ግዜውን የዋጀና ፍቱን ህክምና ለመስጠት ይረዳል፡፡ የአሜሪካ የምግብና ህክምና አስተዳደር እንዲሁ ይህ የፈሳሽ ናሙና ቁራጭ የ EGFR tyrosine kinase inhibitor በራሂ ልውጠት በካንሰር ህዋስ ላይ ሙከራና ምርምር ለማድረግ ያለውን ሚና አይቷል፡፡
 
የሆራይዘን ክልላዊ የካንሰር ማዕከልም በራሱ ይህ አዲስ የህክምና ቴክኖሎጂ ጥቅም ገብቶታል፡፡ በዚህም መሰረት ነው የዚህ የፈሳሽ ህዋስ ናሙና መሳሪያ Thermo Fisher Scientific’s Oncomine™ Pan-Cancer Cell-Free Assay የገዛነው፡፡ በቤት ውስጥ አጠቃላይ የቁራጭ ናሙና ጥናትና ምርምር በማድረግ ፈጣንና ወጭ አልባ(ትንሽ  ወጪ) ያለው ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡ ይህም የህክምና ባለሙያዎች ህክምናውን በግዜ ለመጀመር ይረዳቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሆራይዘን ክልላዊ የካንሰር ማዕክል በታይላንድ የመጀመሪያውና ብጨኛው የመራሄ ማዳቀል የተወሰኑ የካንሰር አየትና ባህርያትን የሚያጠናና የሚመረምር ተቋም ነው፡፡
 

የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና የካንሰርን ህክምና እንዴት ያሻሽላል?

እስከ ቅርብ ጊዜ ይህ የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና እንደ መመርመሪያ የመመርመሪያ መድህኒቶች አጋዥ ሆኖ ብቻ ሆኖ በማገልገል የተወሰነ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ የህክምና ዘዴ ሌሎች የካንሰረ የህክምና ደረጃዎችነ ለማከም ይረዳ ዘንድ ትልቅ ተስፋ አለው፡፡ ለአብነትም የካንሰሩን ደረጃ ቀድሞ ለመለየት ወይንም ምን አይነት  እጢ ሳያወጣ ይህም የሚሆነው የዘረመል ለውጡ በደም ህዋሱ ውስጥ በመኖሩ ነው፡፡
ሌላው የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና ጥቅም ለህክምና ክትትል ይውላል፡፡ ታካሚው በህክምና ሂደቱ ላይ በድንብ ለውጥ ካሳየ በደም ህዋሱ ላይ ያለው የዘረመል ልውጠት ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ይህ የህክምና ዘዴ ታካሚው ሌላ የካንሰር ምልክቶችን እስኪፈጥር ሳይጠበቅ ባለበት ደረጃ ለማከም ይረዳል፡፡ በተለያዩ የአለም አካባቢዎች ያሉ አጥኚዎች በነዚህና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር እያደረጉ ነው፡፡

ይህ የፈሳሽ ቁራጭ ናሙና በካንሰር ህክምና ውስጥ ጠቃሚ ግኝቶችን በማስተዋውቅ ፍጥነት፤ አሳማኝነት እንዲሁም ጥቂት ብቻ የጎኞሽ ጉዳት ያለው በመሆኑ በህክምናው አለም ላይ ትልቅ አሻራ አሳርፏል፡፡ ሁለ ገብነቱ ደግሞ በሚቀጥለው አንድ ወይንም ሁለት አስርት አመታት ደረጃውን የጠበቀ ስነ ተግባር እንዳለው ይመሰክራል፡፡
For more information please contact:
Last modify: ኦክቶበር 30, 2020

Related Packages

Related Health Blogs